ስለ ማህበሩ

ጌዴኦ ልማት ማህበር(ጌልማ) በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በ15 ዞኖች እና በ4 ልዩ ወረዳዎች ውስጥ ከተቋቋሙ የልማት ማህበራት አንዱ ነው።

መግቢያ

የጌዴኦ ልማት ማህበር(ጌልማ) በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል በ15 ዞኖች እና በ4 ልዩ ወረዳዎች ውስጥ ከተቋቋሙ የልማት ማህበራት አንዱ ነው። የማህበሩ ዓላማ (ግዳጅ) ጌዴኦ ማህበረሰብን እድገት ከባለድርሻ አካላት እና ከሌሎች የገንዘብ ተቋማት ጋር በመተባበር የተሻለ ለማድረግ ነው። ይህ ማህበር የተቋቋመዉ ነሐሴ 1988 ሲሆን በ1952 ዓ.ም በተቋቋመው የልማት ማኅበራት አዋጅ 404-82 መሠረት የተመሰረተ ነው።

Agricultural development

ራዕይ

የጌዴኦ ዞን ነዋሪ ሕዝብ በመጪዎቹ 20 ዓመታት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወቱ በትምህርት በተገኘ ዕውቀት፣ ተግባርና ክህሎት አመለካከቱ ተለውጦ፣ ጤንነቱ ተጠብቆ፣ የምግብ ዋስትናው ተረጋግጦ ከአስከፊ ድህነትና ኋላቀርነት ተላቆ ማየት።

ተልዕኮ

የሀገራችንን የእድገት ራዕይና ስትራቴጂ መሠረት በማድረግ እና ሁሉንም የልማት አቅሞችን በማቀናጀት ዘላቂ በሆነ መንገድ የጌዴኦን ዞን ነዋሪ ህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማሳደግ ጠንክሮ በመስራት

እሴቶች

ተጠያቂነት

አሣታፊነት

ግልፀኝነት

ፍትሐዊነት

ተነሳሺነት

ዉጤታማነት

Agricultural development

ዓላማ

  • 1

    በዞኑ ማህበረሰብ ያሉና በመንግሥት ያልተዳሰሱ የሕዝቡ የልማት ጥያቄዎችን መመለስ

  • 2

    በዞኑ የሚገኘውን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሀብት፣ ዕውቀትና ጉልበት ጥቅም ላይ ማዋል

  • 3

    በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርትና በመሠረተ ልማት የኅብረተሰቡን አቅም ማጎልበት

  • 4

    ኋላቀርነትንና ድህነትን በመቀነስ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ

የሎጎአችን ትርጉም

የጌዴኦ ልማት ማህበር ሎጎ የዞኑን ማህበረሰብ፣ ባህል እና የልማት ራዕይ የሚያንፀባርቅ ሲሆን እያንዳንዱ አካል ልዩ ትርጉም ይይዛል።

Gedeo Development Association Logo

የጌዴኦ ልማት ማህበር ሎጎ በዞኑ ውስጥ ዘላቂ ልማትን እና የማህበረሰብ ማጎልበትን ለማምጣት ያለንን ቁርጠኝነት ያሳያል።

የሎጎ ክፍሎችና እና ትርጉማቸው

የጌዴኦ ልማት ማህበር ሎጎ አራት ዋና አካላት ያሉት ሲሆን እያንዳንዱ ልዩ ትርጉም እና ምልክት ይይዛል።

የብርሃን አድማስ
1

የብርሃን አድማስ

የጌዴኦ ልማት ማህበር በአዲስ ተስፋና በተሻጋሪ አስተሳሰብ ብሩህ ወደ ሆነ የብርሃን አድማስ የሚያደርገውን የአጋርነት ወይም የህብረት ጉዞ ያመለክታል።

ሁሉን አቀፍ ልማት
2

ሁሉን አቀፍ ልማት

ለማንኛውም ሃይማኖት፣ ጎሳ፣ ቀለምና የፖለቲካ አመለካከት ሳይወግን ሁሉን አቀፍ ልማት ማህበረሰቡን በእውቀት፣ በጉልበት፣ በገንዘብና ቁሳዊ በሆነ ሃብት በማስተሳሰር የሚተጋ የልማት ማህበር መሆኑን ያመለከታል።

የአጋርነት ጉዞ
3

የአጋርነት ጉዞ

የሰዎች በአጋርነት፣ በመተባበርና በመተጋገዝ አንድ ዓላማና አጋር ራዕይ እንግበው ልዩነታቸውን አጋዥ መሳሪያ በመጠቀም የሚያደርጉትን ሁሉን አቀፍ የተቀናጀ የእድገት ጉዞ ያመለክታል።

ቀጣይነት ያለው ልማት
4

ቀጣይነት ያለው ልማት

ቀጣይነት ያለው፣ ያልተቋረጠ፣ የእድገት ስብጥር ያለው አጋር ዓላማ ከፍ ወዳለ እድገት የሚደረግ ሁሉን አቀፍ፣ የሁሉም ተሳትፎና ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ወደ ልማት የሚደረግ ጉዞን ያመለክታል።

የድርጅታዊ መዋቅር

የድርጅታችን መዋቅር በተለያዩ ደረጃዎች የተደራጀ ሲሆን እያንዳንዱ አካል የተለየ ሚና እና ኃላፊነት አለው።

ጠቅላላ ጉባኤ

የድርጅቱ ከፍተኛ የውሳኔ አካል

ዋና ኃላፊነቶች

1

የድርጅቱን ዓመታዊ እቅድ እና በጀት መገምገም እና ማፅደቅ

2

የድርጅቱን ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች መቅረፅ

3

የማኔጅመንት ቦርድ አባላትን መምረጥ

4

የድርጅቱን አፈፃፀም መገምገም

5

የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻል

የማኔጅመንት ቦርድ

የድርጅቱን ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር አካል

ዋና ኃላፊነቶች

1

የድርጅቱን ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መቆጣጠር

2

የጠቅላላ ጉባኤ ውሳኔዎችን ማስፈፀም

3

ዋና ሥራ አስፈጻሚ መቅጠር እና መቆጣጠር

4

የድርጅቱን ፕሮጀክቶች መገምገም

5

ለጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት ማቅረብ

ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የድርጅቱን ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚመራ ሰው

ዋና ኃላፊነቶች

1

የድርጅቱን ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ መምራት

2

የሰው ሀይል አስተዳደር

3

የፕሮጀክት አፈፃፀምን መቆጣጠር

4

ከአጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት መፍጠር

5

ለማኔጅመንት ቦርድ ሪፖርት ማቅረብ

የሂሳብ ኮሚቴ

የድርጅቱን የፋይናንስ አስተዳደር የሚቆጣጠር አካል

ዋና ኃላፊነቶች

1

የድርጅቱን የፋይናንስ አስተዳደር መቆጣጠር

2

የውስጥ ኦዲት ማካሄድ

3

የፋይናንስ ሪፖርቶችን መገምገም

4

የፋይናንስ አሰራሮችን መከታተል

5

ለጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት ማቅረብ

ዋና ጽሕፈት ቤት

የድርጅቱን ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ የሚያስፈፅም አካል

ዋና ኃላፊነቶች

1

የድርጅቱን ዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ማስፈፀም

2

የፕሮጀክት ትግበራ

3

ሀብት አሰባሰብ

4

የሰው ሀይል አስተዳደር

5

የፋይናንስ አስተዳደር

6

ከአጋር ድርጅቶች ጋር ግንኙነት መፍጠር

የአመራር ተዋረድ

የድርጅታችን የአመራር ተዋረድ ከጠቅላላ ጉባኤ ጀምሮ እስከ አፈፃፀም ደረጃ ድረስ የተደራጀ ነው።

ጠቅላላ ጉባኤ

ከፍተኛ ባለሥልጣን

የማኔጅመንት ቦርድ

የአመራር አካል

ዋና ሥራ አስፈጻሚ

የዕለት ተዕለት አስተዳደር

የሂሳብ ኮሚቴ

የቁጥጥር አካል

ዋና ጽሕፈት ቤት

የአፈፃፀም አካል