ሁሉን አቀፍ ልማት ለዘላቂ እድገት

አብረን ከተባበርን
እንችላን!

በትምህርት፣ ጤና፣ ዉሃ፣ በመሠረተ-ልማት ግንባታና በሌሎች ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎች የማህበረሰባችንን ሕይወት ማሻሻል!

የማህበረሰቡ ህጻናት እየሳቁ እና የሰላም ምልክት እየሰጡገደብ ትምህርት ቤትገደብ ትምህርት ቤትራጴ ትምህርት ቤትየመዝናኛ ማዕከልዳራሮ ትምህርት ቤትዳራሮ ትምህርት ቤትየእርሻ ፕሮጀክት 2የእርሻ ፕሮጀክት 3የባህል እንቅስቃሴየባህል እንቅስቃሴ 2
የልማት ማህበሩ አባል በመሆን የለውጡ አካል ይሁኑ

የአባልነት ማዕቀፎች ለግለሰቦች፣ ለግል ድርጅቶች እና ለመንግሰት ተቋማት

የልማት ማህበሩ አባል በመሆን የለውጡ አካል ይሁኑ

የግለሰብ አባልነት

የግለሰብ አባልነት

ከቀረቡ የአባልነት አማራጮች በምረጥና አባ በመሆን የለዉጡ አካል ይሁኑ

የግል ድርጅት

የግል ድርጅት

ለማህበረሰብ ልማት ቁርጠኛ ለሆኑ የግል ድርጅቶች

የመንግስት ተቋማት

የመንግስት ተቋማት

ከመንግስት ተቋማት ጋር የትብብር ማዕቀፍ

የልማት ማህበሩ ራዕይ እና ተልዕኮ

ስለ ጌዴኦ ልማት ማህበር

ጌዴኦ ልማት ማህበር (ጌልማ) በዞኑ ውስጥ ዘላቂ ልማትን ለማምጣት እና የማህበረሰቡን የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል የሚሰራ ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው።

ራዕይ

የጌዴኦ ዞን ነዋሪ ሕዝብ በ2030 ዓ.ም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ህይወቱ በትምህርት በተገኘ ዕውቀት ተግባርና ክህሎት አመለካከቱ ተለውጦ ጤንነቱ ተጠብቆ የምግብ ዋስትናው ተረጋግጦ ከአስከፊ ድህነትና ኋላ ቀርነት ተላቆ ማየት ራዕያችን ነው።

ተልዕኮ

ሁሉንም የልማት አቅም በማቀናጀት ዘላቂ በሆነ መንገድ የዞኑ ነዋሪ ህዝብ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊና በሌሎች የልማት ዘርፎች ለማሳደግ ጠንክሮ በመስራት ከተለያዩ የሀብት ምንጮች ገቢ እየሰበሰበ የልማት ፍላጎቶችን ለማሟላት መሥራት ነው፡፡

በክፍል ውስጥ ያሉ ልጆች
View Project

አጀማመር

ጌዴኦ ልማት ማህበር በ1990ዎቹ መጀመሪያ ከደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ልማት ማህበር ክፍል ሆኖ ተጀመረ። በኋላም ሙሉ ሥልጣን አግኝቶ ነፃ የሕግ ማንነት እና የራሱን የአስተዳደር መዋቅር አገኘ።

ድርጅቱ በኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት ኤጀንሲ የተመዘገበ ሲሆን የክርስቲያናዊ እርዳታ እና ልማት ማኅበራት ኮንሶርሺየም አባል ነው።

ድርጅቱ በሀገራዊ ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች በመመራት በጌዴኦ ዞን ውስጥ የኑሮ ደረጃን ለማሻሻል የሚያስችሉ ጥናቶችን መሠረት በማድረግ ስራዎችን አከናውኗል።

ተደራሽነት

ልማት ማህበሩ ለተቋቋመበት አላማ ከምን ጊዜዉም በላይ በመትጋት ዉጤት በማስመዝገብ ላይ ይገኛል!

27+

አመታትን

ማህበረሰቡን አገልግሏል

500,000+

አባላት

የልማት ማህበሩ አጋር ናቸዉ

140+

የማህበረሰብ

ፕሮጀክቶችን አከናዉኗል

1,000,000+

ተደራሽ በማድረግ

የበኩሉን በመወጣት ላይ ይገኛል

ፕሮግራሞቻችን

በማህበረሰቡ ውስጥ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት በተለያዩ ዘርፎች ጠንካራ የሚባል እንቃስቃሴ በማከናወን ላይ ይገኛል

Educated Man Power
ትምህርት እና ስልጠና

የተማረ የሰው ሃይል

ዘላቂ ልማት ለማምጣት የሚያስችል የተማረ የሰው ሃይል በትምህርት፣ በስልጠና ፕሮግራሞች እና በአቅም ግንባታ ተነሳሽነቶች በኩል ማዳበር።

Infrastructure Building
የልማት ፕሮግራም

የመሰረተ ልማት ግንባታ

ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለመደገፍ እና የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ መንገድና የማህበረሰብ ማዕከላትን ጨምሮ አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት በመስራት ላይ ይገኛል።

Capacity Building
የማብቃት ፕሮግራም

አቅም ግንባታ

በተለያዩ ዘርፎች ዘላቂ ልማትን እና ራስን መቻልን ለማረጋገጥ የአካባቢ ተቋማትን አቅም ማጠናከር።

የተማረ የሰው ኃይል

የትምህርት ያለፈ ሰው ኃይልን ለማሳደግ ያለው መሠረታዊ ራእይ አማካኝነት፣ ጌዴኦ ልማት ማህበር ከ26 ዓመታት በላይ ባለፈው ጊዜ ባለብዙ ደረጃ የትምህርት ድጋፍ ፕሮጄክቶችን ተግብሮ ይገኛል። ፕሮጄክቶቻችን በሁሉም ደረጃ ሊቃውንት እንዲያፈሩ በማሰብ የተዘጋጁ ናቸው

ደራሮ አዳሪ ትምህርት ቤት

በትምህርት አቅርቦት ላይ እንደ አንድ ጉልህ ምዕራፍ በሚቆጠር መልኩ፣ ደራሮ አዳሪ ትምህርት ቤት ከጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ 212 ተማሪዎችን በመቀበል በይፋ ተመርቆ የመማር ማስተማር ሥራውን ጀምሯል፡፡ ይህ ታላቅ ምዕራፍ ሊሳካ የቻለው የጌዴኦ ዞን አስተዳደር፣ የጌዴኦ ልማት ማህበር፣ የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በቀድሞው የሆስቴል ማዕከል ላይ በአጭር ጊዜ መማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣ የመመገቢያ አዳራሽ ግንባታ፣ የተጠናከረ የአጥር ግንባታ፣ የሴቶች እና ወንዶች ዶርሚተሪ ክፍሎችን ሙሉ እደሳ እንዲሁም ዘመናዊ የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ላብራቶሪ ማቋቋምን አካቷል፡፡ ከዚህም ባሻገር ልማት ማህበሩ፤ ትምህርት ቤቱ ብቁ መምህራንን፣ የአስተዳደርሠራተኞች እና ለስኬታማ የመማር ማስተማር ሂደት ምቹና አበረታች አከባቢ ለመፍጠር የሚያስፈልጉ ሌሎች ወሳኝ ግብዓቶች በሙሉ እንዲሟሉ አድርጓል፡፡

ዲላ ከተማ
ዳራሮ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

ሆስቴል ተማሪዎች ፕሮጀክት

ሆስቴል ተማሪዎች ፕሮጀክት

የጌዴኦ ልማት ማህበር ባለፉት 26 ዓመታት እስከ 2016 ዓ.ም ድረስ የተማሪዎች ማደሪያ፣ ምግብ፣ የጤና አገልግሎት እና የትምህርት ክፍያን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል፤ ይህም ማህበረሰቡን የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት አግዟል።

የትምህርት ድጋፍ

የመጀመሪያ ዲግሪ ድጋፍ

የመጀመሪያ ዲግሪ ድጋፍ

የጌዴኦ ልማት ማህበር በድላ ዩኒቨርሲቲ እና በሌሎች ተቋማት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን የትምህርት ክፍያ እና ሌሎች የትምህርት ወጪዎችን በመሸፈን ያስምራል፤ ይህም ማህበረሰቡን በተማረ የሰው ኃይል የማብቃት ራዕዩን እዲያሳካ አድርጎታል።

የከፍተኛ ትምህርት

የሁለተኛ ዲግሪ ድጋፍ

የሁለተኛ ዲግሪ ድጋፍ

ከመጀመሪያ ዲግሪ ድጋፍ ጋር በሚመሳሰል መልኩ፣ የጌዴኦ ልማት ማህበር የማስተርስ ተማሪዎችን የትምህርት ክፍያ በመሸፈን ድጋፍ ያደርጋል፤ ይህም ማህበረሰቡን በተማረ የሰው ኃይል ለማብቃት ነው።

የማስተርስ ዲግሪ

የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎች

የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎች

የጌዴኦ ልማት ማህበር በተለያዩ የአገር ዉስጥ እና አለም አቀፍ የትምህርት ተቋማት የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎችን የትምህርት ክፍያ በመሸፈን ያስምራል፤ ይህም ማህበረሰቡን በተማረ የሰው ኃይል የማብቃት ራዕዩን ያጠናክራል።

የዶክትሬት ዲግሪ

በቅርብ ጊዜ ከተከናወኑ ፕሮጀክቶችን በጥቂቱ

በዞኑ በሚገኙ ወረዳወች እና ከተማ አስተዳደሮች ላይ ከተከናወኑ ፕሮጀክቶች መካከል በጥቂቱ ይመልከቱ

የትምህርት መሰረተ ልማት

የቡሌ ከተማ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት

6 የመማሪያ ክፍሎች፣ የአስተዳደር ቢሮዎች እና መጸዳጃ ቤቶች ያሉት ሲሆን በአንድ ጊዜ 300 ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ነዉ።

ቡሌ ወረዳ ትምህርት ቤት
ቡሌ ወረዳ

የገደብ ከተማ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት

በ2023 ተጠናቀቀ እና በአንድ ጊዜ ከ300 በላይ ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚችል ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት በልማት ማህበሩ ተገንብቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ገደብ ከተማ ትምህርት ቤት
1/4 Photos
ገደብ ከተማ
ምስሎችን ይመልከቱ

የአፄ ዳዊት ትምህርት ቤት ማስፋፊያ

በአጼ ዳዊት ትምህርት ቤት ያለዉን የክፍል ጥበት ለመቅረፍ ማስፋፊያ አንድ ብሎክ ሕንጻ ተገንብቶ ነሐሴ 20/2015 ዓ.ም ርክክብ ተደርጓል።

የዲላ ከተማ አፄ ዳዊት ትምህርት ቤት ማስፋፊያ
1/3 Photos
ዲላ ከተማ

የራጴ ወረዳ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት

የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት ግንባታ ተከናዉኖ የካቲት 23/2016 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎ በመስጠት ላይ ይገኛል።

የራጴ ወረዳ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት
1/5 Photos
ራጴ ወረዳ

የባንቆ ኦኮቶ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት

የባንቆ ኦኮቶ 1ኛ ደረጃ ትምህት ቤት 4 ብሎክ ሕንጻ ግንበታዉ ተጠናቆ አገልግት በመስጠት ላይ ይገኛል።

የወናጎ ወረዳ ባንኮ ኦኮቶ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
1/2 Photos
ወናጎ ወረዳ

የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል

የጨለለቅቱ ከተማ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል

የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ግንባታዉ ተጠናቆ አገልግት በመስጠት ላይ ይገኛል።

የጨለለቅቱ ከተማ የቁም እንስሳት ገበያ ማዕከል
ጨለለቱ ከተማ

የጮርሶ ወረዳ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል

የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ግንባታዉ ተጠናቆ አገልግት በመስጠት ላይ ይገኛል።

የጮርሶ ወረዳ የቁም እንስሳት ገበያ ማዕከል
ጮርሶ ወረዳ

ጤና እና የሕክምና ተቋማት

የጪጩ ጤና ጣቢያ ማስፋፊያ

የወላዶችን የጤና አገልግሎቶችን ለማሻሻል እና የመውለጃ ክፍሎች ቦታ ጥበትን አንዲያስችለል ልማት ማህበሩ ለዚሁ አገልግሎት የሚዉን አንድ ብሎክ ህንጻ ገንብቶ ለአገልግሎት አብቅቷል።

ከተባበርን እንችላለን
ተጠናቅቋል
የጪጩ ጤና ጣቢያ ማስፋፊያ

የእርሻ ፕሮጀክቶች

የእርሻ ፕሮጀክቶች

በሂደት ላይ

የእርሻ ፕሮጀክቶች፣ በአሁኑ ወቅት ስንዴ፣ በቆሎ እና እንደ ድንች ያሉ አትክልቶችን በማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የበኩሉን በመወጣት ላይ ይገኛል።

ከተባበርን እንችላለን
በሂደት ላይ
የእርሻ ፕሮጀክት 1
የእርሻ ፕሮጀክት 2
የእርሻ ፕሮጀክት 3
የእርሻ ፕሮጀክት 4
የእርሻ ፕሮጀክት 5
የእርሻ ፕሮጀክት 6
የእርሻ ፕሮጀክት 7
የእርሻ ፕሮጀክት 8
የእርሻ ፕሮጀክት 9
የእርሻ ፕሮጀክት 10

ለውጥ ለማምጣት ከእኛ ጋር ይተባበሩ

ከተባበርን እንችላለን።

የጌዴኦ ማህበረሰብ ልጆች